የበሽታ ቅኝት...

ዝርዝር ዜና

አቃቂ ቃሊቲ ጤና ፅ/ቤት

የበሽታ ቅኝት

ሚያዝያ 16-2018
ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ

በጤና ተቋማት ውስጥ የተቀናጀ የበሽታ ቅኝትና ምላሽ (IDSR) አተገባበርን ማጠናከር ያስፈልጋል። አ/አ/ጤና ቢሮ ሚያዚያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጤና ስጋቶችን አስቀድሞ በመለየትና ምላሽ በመስጠት አበረታች ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። ቢሮው ሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭስ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በተለይም ፕሮጀክቱ ተደራሽ ባደረገባቸው ክፍለ ከተሞችና ጤና ጣቢያዎች የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል። ስራውን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከመንግስት የጤና ተቋማት በተጨማሪ የግል የጤና ተቋማት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ፣ የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ፣ ሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭስ እና ፕሮጀክቱ በቀጣይ ተደራሽ የሚያደርጋቸው በመዲናዋ የሚገኙ የግል የጤና ተቋማት በጋራ ውይይት አካሂደዋል። ​ትብብርን በማጎልበት ፣ የጤና ስጋቶችን ቀድሞ በመለየት እና ምላሽ በመስጠት ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋት በመዲናዋ በሚገኙ ሁሉም የጤና ተቋማት የተቀናጀ የበሽታ ቅኝትና ምላሽ (IDSR) አተገባበርን በማጠናከር የጤና ስርዓቱን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ በውይይቱ ተገልጿል። በውይይቱ በግል ጤና ተቋማት የተቀናጀ የበሽታ ቅኝትና ምላሽ (IDSR) አተገባበርን ለማጠናከር የሚያስችል ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን ለውጦች መመዝገብ መቻላቸው ተመላክቷል። በመጀመሪያው ምዕራፍ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በሁለተኛው ምዕራፍ ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል ​በመንግሥት እና በግል የጤና ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር በማሳደግ በመዲናዋ በዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ እንደሚሰራ በውይይቱ ተነግሯል። ለፕሮግራሙ ስኬታማነት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በተጨማሪ የሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭስ ፣ የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን እና የግል የጤና ተቋማት አሰሪዎች ማህበር ሚና ከፍተኛ መሆኑም ተጠቁሟል።